Svensk-Etiopiska föreningen är en opolitisk, religiöst obunden vänskapsförening som bildades i Stockholm 1952. De breda och djupa kontakterna mellan Sverige och Etiopien, som grundlades redan på 1950-talet, är basen och den gemensamma bakgrunden för föreningens medlemmar. Även etiopier bosatta i Sverige har tillfört föreningen ökad kunskap och förståelse för Etiopien, dess land och folk.
Folkhälsomyndigheten har information om Covid-19 och nya coronoviruset på många språk språk däribland Amhariska, Tigrinja, Somaliska och Arabiska.
Klicka på denna länk: https://www.folkhalsomyndigheten.se/smittskydd-beredskap/utbrott/aktuella-utbrott/covid-19/skydda-dig-och-andra/information-pa-olika-sprak/
ራስዎንና ሌላውን በሽታ ከማስተላለፍ ይከላከሉ
Skydda dig och andra från smittspridning på amhariska.
ከታማሚው ሰው ጋር የቀረበ ግንኙነት ከማድረግ ይቆጠቡ። በመካያው ራስዎንና ሌላውን በበሽታው ከመጠቃት ይከላከላሉ።
በዚህ መረጃ፥ ራስዎን ከመለከፍ እንዴት መከላከል እንዳሚችሉ ብዙ ምክር እንሰጣለን።
ከታመሙ ከቤት አይውጡ
የታመሙ ከመሰልዎትና የአፍንጫ ፈሳሽ፥ ሳል ወይም ትኩሳት ካለብዎት ከሥራ ቀርተው ቤት ይዋሉ። ይህን ሲያደርጉ በሽታውን ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፉ ዕድ አይኖርም ማለት ነው። ህመምዎ አነስተኛ መስሎ ቢሰማዎትም ይህን ማድረግ ይኖርብዎታል።
ከህመሙ ያልዳኑ መስሎ እስከተሰማዎት ድረስ ከቤት አይውጡ። ህመሙ እየጠናብዎ ከሄደና እቤትዎ ውስጥ ራስዎን መንከባከብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ከደረሱ 1177 በመደወል ከጤና ባለሙያዎች ጋር (በእንግሊዝኛ ወይም በስዊድንኛ) መነጋገር ይችላሉ።
ከበሽታው ከተፈወሱ በኋላ ቢያንስ ሁለት ድፍን ቀናት ወደ ትምህርት ቤትም ሆነ ወደ ሥራ ሳይሄዱ ይቆዩ።
በዕድሜ ጠና ያሉ ሰዎች በበሽታው ክፉኛ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ስለሆነም በሆስፒታል ተኝተው ህክምና የሚከታተሉትና በአረጋዊያን መንከባከቢያ መኖሪያዎች ያሉት አረጋዊያን፥ እንዲያው ግድ ካልሆነ በቀር መጠየቅ አያስፈልግም። ትንሽ ህመም የሚሰማዎት ከሆነ ደግሞ ጭራሹን ወደነዚህ ቦታዎች ዝር አይበሉ። የአረጋዊያን ጤና ጥበቃ ሥራ የምትሠሰሩ ሰዎች፥ የሚያስላችሁ ከሆነ ወይም ጉንፋን ነገር ከያዛችሁ ወደ ሥራ ቦታ መሄድ የለባችሁም።
የኮቪድ -19ን ምልክቶች አጥነው ልብ ይበሉ
የኮቪድ- 19 ህመም ዋናዎቹ ምልክቶች ትኩሳትና ሳል ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ፥ የትንፋሽ ማጠር፣ የአፍንጫ ፈሳሽ፥ የጉሮሮ ህመም፥ ራስምታት፥ የጡንቻና መገጣጠሚያ ህመም የተለመዱ ናቸው። የዚህ በሽታ ተጠቂዎች በአብዛኛው መጠነኛ ህመም ሲኖርባቸው በራሳቸው ግላዊ እንክብካቤ ብቻ ድነው ይወጣሉ። ብዙዎች ደግሞ ለከፋ ህመም ይዳረጋሉ፥ የመተንፈስ ችግርና የሳምባ መበከል ሁሉ ሊደርስባቸው ይችላል። እንዲህ ዓይነት ምልክቶች ከታዩቦት ሌሎች ሰዎችን ከማግኘት በእጅጉ ይቆጠቡ።
እጆችዎን በተደጋጋሚ ይታጠቡ
የኮሮና ቫይረስን የሚያራባው ንጥረነገር ከአንድ አካል ወደ ሌላ የመተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ ሲሆን እጆች ላይ በቀላሉ የመላከክምባህሪ አለው። በዚህ ምክንያት ሌላን ሰው በእጅዎ ሲነኩት ወደ ተንካው ሰው ይተላለፋል። ስለዚህ እጅዎችዎን በሳሙና እና በሙቅ ውሃ ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች መታጠብ አስፈላጊ ነው።
እጅዎችዎን ሁሌ ይታጠቡ፣ወደ ቤትዎ ሲገቡ ወይም ወጭ ቆይተው ወደ ሥራ ቦታ ሲመጡ፥ ምግብ ከመመገብዎ በፊት፥ የሚበላ ነገር ከመነካካትዎ በፊት፥ እንዲሁም መጸዳጃ ስፍራን ጎብኝተው ሲጨርሱ እጆችዎን በሳሙናና በሙቅ ውሃ መታጠብ አይዘንጉ።
እጆችዎን መታጠብ የማይችሉበት ሁኔታ ካለ፥ የእጅ አልኮልን እንደ ሌላ አማራጭ በውሰድ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
ክንድ መታጠፊያ ላይ መሳል እና ማነጠስ
ሲስሉ ወይም ሲያነጥሱ ተላላፊ ነገሮችን የተሸከሙ በጣም ጥቃቅን የሆኑ ጠብታዎች በዓየር ላይ ይሰራጩ እና ቫይረሱን በአካባቢው ባሉ ነገሮች ላይ ማዛመት ይችላሉ። የክንድ መታጠፊያ ላይ በማሳል ወይም በማነጠስ፣ እንዲሁም የአፍንጫ መጥረጊያ ወረቀት ላይ በማሳል ወይም በማነጠስ ቫይረሱ ወደ አካባቢዎ ወይም ወደ እጅዎ እንዳይሻገር መከላከል ይችላሉ። የተጠቀሙበትን የአፍንጫ መጥረጊያ ሁሌ በቆሻሻ መጣያ እቃ ላይ ይጣሉ፥ በዚያው እጆችዎንም ይታጠቡ።
ዐይንዎን፥ አፍንጫዎንና አፍዎን ከመንካት መቆጠብ
በሽታው የሚተላለፈው ዐይን ውስጥ፥ አፍንጫና አፍ ውስጥ ባለው የውስጥ ሥጋ ወይም አካል በኩል ነው። ስለዚህ ዐይንዎን፥ አፍንጫዎንና አፍዎን በእጆዎ ከመንካት ይቆጠብቡ።
የእጅ አልኮል
ሳሙና እና ውሃ ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ካሉ፥ 60 % አልኮል መጠን ባለው የእጅ አልኮል መጠቀም ይችላሉ።
Källa: Folkhälsmyndigheten
Utbildning är en av de viktigaste faktorerna för att ta sig ur fattigdom.
För att kunna tillgodogöra sig utbildning behöver barn tillräckligt med näring.
I stora delar av världen saknar föräldrarna möjlighet att ge sina barn tillräckligt med mat.
Svensk-Etiopiska Föreningen ger elever i förskolan Firehiywet, Addis Abeba, Etiopien, frukost
varje skoldag sedan ett år tillbaka.
Lärarna och föräldrarna märker stor skillnad på barnens förmåga att följa undervisningen.
Motivationen att komma till skolan har ökat och barnen blir även lugnare, med mat i magen.
Du kan bidra till att skapa förutsättningar för fler att förbättra sina liv.
Skicka i så fall ett bidrag till följande bankkonto:
Clearingnummer 8381-6
Kontonummer 693 500 629-3
(Swedbank, Svensk-Etiopiska Föreningen)
Bidraget får gärna vara månatligt
Ange ert namn som meddelande (OBS max 10 tecken)
Vi kommer kontinuerligt att visa information på hemsidan.
Varje frukost kostar idag ca 5 SEK.