Folkhälsomyndigheten har information om Covid-19 och nya coronoviruset på många språk språk däribland Amhariska, Tigrinja, Somaliska och Arabiska.
Klicka på denna länk: https://www.folkhalsomyndigheten.se/smittskydd-beredskap/utbrott/aktuella-utbrott/covid-19/skydda-dig-och-andra/information-pa-olika-sprak/

 

ራስዎንና ሌላውን በሽታ ከማስተላለፍ ይከላከሉ
Skydda dig och andra från smittspridning på amhariska.

ከታማሚው ሰው ጋር የቀረበ ግንኙነት ከማድረግ ይቆጠቡ። በመካያው ራስዎንና ሌላውን በበሽታው ከመጠቃት ይከላከላሉ።
በዚህ መረጃ፥ ራስዎን ከመለከፍ እንዴት መከላከል እንዳሚችሉ ብዙ ምክር እንሰጣለን።

ከታመሙ ከቤት አይውጡ
የታመሙ ከመሰልዎትና የአፍንጫ ፈሳሽ፥ ሳል ወይም ትኩሳት ካለብዎት ከሥራ ቀርተው ቤት ይዋሉ። ይህን ሲያደርጉ በሽታውን ወደ ሌላ ሰው የማስተላለፉ ዕድ አይኖርም ማለት ነው። ህመምዎ አነስተኛ መስሎ ቢሰማዎትም ይህን ማድረግ ይኖርብዎታል።

ከህመሙ ያልዳኑ መስሎ እስከተሰማዎት ድረስ ከቤት አይውጡ። ህመሙ እየጠናብዎ ከሄደና እቤትዎ ውስጥ ራስዎን መንከባከብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ከደረሱ 1177 በመደወል ከጤና ባለሙያዎች ጋር (በእንግሊዝኛ ወይም በስዊድንኛ) መነጋገር ይችላሉ።

ከበሽታው ከተፈወሱ በኋላ ቢያንስ ሁለት ድፍን ቀናት ወደ ትምህርት ቤትም ሆነ ወደ ሥራ ሳይሄዱ ይቆዩ።

በዕድሜ ጠና ያሉ ሰዎች በበሽታው ክፉኛ የመጠቃት ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ስለሆነም በሆስፒታል ተኝተው ህክምና የሚከታተሉትና በአረጋዊያን መንከባከቢያ መኖሪያዎች ያሉት አረጋዊያን፥ እንዲያው ግድ ካልሆነ በቀር መጠየቅ አያስፈልግም። ትንሽ ህመም የሚሰማዎት ከሆነ ደግሞ ጭራሹን ወደነዚህ ቦታዎች ዝር አይበሉ። የአረጋዊያን ጤና ጥበቃ ሥራ የምትሠሰሩ ሰዎች፥ የሚያስላችሁ ከሆነ ወይም ጉንፋን ነገር ከያዛችሁ ወደ ሥራ ቦታ መሄድ የለባችሁም።

የኮቪድ -19ን ምልክቶች አጥነው ልብ ይበሉ
የኮቪድ- 19 ህመም ዋናዎቹ ምልክቶች ትኩሳትና ሳል ናቸው። ከዚህ በተጨማሪም ፥ የትንፋሽ ማጠር፣ የአፍንጫ ፈሳሽ፥ የጉሮሮ ህመም፥ ራስምታት፥ የጡንቻና መገጣጠሚያ ህመም የተለመዱ ናቸው። የዚህ በሽታ ተጠቂዎች በአብዛኛው መጠነኛ ህመም ሲኖርባቸው በራሳቸው ግላዊ እንክብካቤ ብቻ ድነው ይወጣሉ። ብዙዎች ደግሞ ለከፋ ህመም ይዳረጋሉ፥ የመተንፈስ ችግርና የሳምባ መበከል ሁሉ ሊደርስባቸው ይችላል። እንዲህ ዓይነት ምልክቶች ከታዩቦት ሌሎች ሰዎችን ከማግኘት በእጅጉ ይቆጠቡ።

እጆችዎን በተደጋጋሚ ይታጠቡ
የኮሮና ቫይረስን የሚያራባው ንጥረነገር ከአንድ አካል ወደ ሌላ የመተላለፍ አቅሙ ከፍተኛ ሲሆን እጆች ላይ በቀላሉ የመላከክምባህሪ አለው። በዚህ ምክንያት ሌላን ሰው በእጅዎ ሲነኩት ወደ ተንካው ሰው ይተላለፋል። ስለዚህ እጅዎችዎን በሳሙና እና በሙቅ ውሃ ቢያንስ ለ20 ሴኮንዶች መታጠብ አስፈላጊ ነው።

እጅዎችዎን ሁሌ ይታጠቡ፣ወደ ቤትዎ ሲገቡ ወይም ወጭ ቆይተው ወደ ሥራ ቦታ ሲመጡ፥ ምግብ ከመመገብዎ በፊት፥ የሚበላ ነገር ከመነካካትዎ በፊት፥ እንዲሁም መጸዳጃ ስፍራን ጎብኝተው ሲጨርሱ እጆችዎን በሳሙናና በሙቅ ውሃ መታጠብ አይዘንጉ።

እጆችዎን መታጠብ የማይችሉበት ሁኔታ ካለ፥ የእጅ አልኮልን እንደ ሌላ አማራጭ በውሰድ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ክንድ መታጠፊያ ላይ መሳል እና ማነጠስ
ሲስሉ ወይም ሲያነጥሱ ተላላፊ ነገሮችን የተሸከሙ በጣም ጥቃቅን የሆኑ ጠብታዎች በዓየር ላይ ይሰራጩ እና ቫይረሱን በአካባቢው ባሉ ነገሮች ላይ ማዛመት ይችላሉ። የክንድ መታጠፊያ ላይ በማሳል ወይም በማነጠስ፣ እንዲሁም የአፍንጫ መጥረጊያ ወረቀት ላይ በማሳል ወይም በማነጠስ ቫይረሱ ወደ አካባቢዎ ወይም ወደ እጅዎ እንዳይሻገር መከላከል ይችላሉ። የተጠቀሙበትን የአፍንጫ መጥረጊያ ሁሌ በቆሻሻ መጣያ እቃ ላይ ይጣሉ፥ በዚያው እጆችዎንም ይታጠቡ።

ዐይንዎን፥ አፍንጫዎንና አፍዎን ከመንካት መቆጠብ
በሽታው የሚተላለፈው ዐይን ውስጥ፥ አፍንጫና አፍ ውስጥ ባለው የውስጥ ሥጋ ወይም አካል በኩል ነው። ስለዚህ ዐይንዎን፥ አፍንጫዎንና አፍዎን በእጆዎ ከመንካት ይቆጠብቡ።

የእጅ አልኮል
ሳሙና እና ውሃ ማግኘት የማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ካሉ፥ 60 % አልኮል መጠን ባለው የእጅ አልኮል መጠቀም ይችላሉ።

Källa: Folkhälsmyndigheten 

Minnes & Högtidsgåvor

högtidsgåvaMHY Sida 1
 Stöd föreningens projekt "Ett mål om dagen"
med en minnes eller högtidsgåva.
Bilderna levereras på kraftigt papper i A4-format.
Klicka på bilden ovan för att se fler exempel
eller göra en beställning

Info på Amahariska

የስዊድናዊያንና-የኢትዮጵያውያን ማህበር በ 1952 ስቶክሆልም ውስጥ የተቋቋመ ከፖለቲካ: ከሃይማኖትና ከወገንተኛነት ነጻ የሆነ የወዳጅነት ማህበር ነው:

ወደ የስዊድናዊያንና-የኢትዮጵያውያን የወዳኝነት ማህበር እንኩዋን በደህና መጡ!

እርስዎና ቤተሰብዎ የስዊድናዊያንና-የኢትዮጵያውያን የወዳኝነት ማህበር አባል ሆነው እንድትመዘገቡ በትህትና ተጋብዘዋል

ማህበሩ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የሚደግፍ ከመሆን አልፎ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የንግድና የባህል ልውውጥ እንዲበልጽግ የሚያመቻች መድረክና መገናኛ ቦታ ነው

አባል በመሆን በኢትዮጵያ ባህልና ማህበራዊ ኑሮ: በተፈጥሮ ሃብትና በንግድ መስክ እውቀትና ልምድ ባለው የማህበሩ መድረክ ተካፋይና ተሳታፊ ይሆናሉ

በአባልነት ለመመዝገብ: www.svensk-etiopiska.se ገብተው ይመዝገቡና የአባልነት ክፍያ በመክፈል የማህበሩ ጋዜጣ ቤትዎ ይላክልዎት ዘንድ አድራሻዎን ይመዝግቡ::

Styrelse

                    Styrelse
Ordförande:         Biniyam Wondimu

Vice ordf.               Håkan Pohlstrand
Sekreterare:         Michael Ståhl
Kassör:                   Per Wallgren
Medlemssekr:      Örjan Åkerrén
Ledamöter:           Wessen Beshah
                                   Sven Britton
                                   Jan Olof Gustavi
                                   Ingegerd Nylander
                                   Sonja Pohlstrand
Suppleant:             Lydia Watchefo
                                   
Webb/Facebook: Martin Hydén

Org.nr:                     802004-5657

Kontakt e-post:     
kontakt@svensk-etiopiska.se 
eller via kontaktformulär

Vår Facebooksida:

Betala med Swish

   Medlemsavgift 2024

medl2023

  Bidrag till måltidsprojektet 

QR maltid 2023

      Mer om Swishbetalning